Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል  በከተሞች የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻ በወላይታ ሶዶ  የችግኝ ተከላ መርሃግብር  ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በደቡብ ክልል በከተሞች የአረንጓዴ አሻራ ቀንን ለማሳረፍ የሚያስችል መርሃ ግብር በዛሬው ዕለት በወላይታ ሶዶ ከተማ ተጀምሯል፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ድኤታ ወይዘሮ መሠረት መስቀሌ በመርሃግብሩ ላይ የተገኙ ሲሆን÷ የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻው አገራችን የብዝሃ ህይወት ሃብትን ለማስጠበቅና የአካባቢ የአየር ብክለትን ለመከላከል ፋይዳው ከፍተኛ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

በአገሪቱ ባሉ ሁሉም ከተሞች አንድ ቢሊየን ችግኝ እንደሚተከልም ጠቁመዋል፡፡

በደቡብ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ  ÷የአካባቢ ጥበቃ ለአረንጓዴው ኢኮኖሚያችን ዋስትና መሆነን ተናግረው በክልሉ ሁሉም ከተሞች ከ150 ሚሊዮን በላይ ችግኝ እንደሚተከል ተናግረዋል፡፡

የሶደ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ያለው ጌታቸው በበኩላቸው÷ በከተሞች የሚደረጉ የአረንጓዴ አሻራ ስራዎች በአየር ብክለት ሳቢያ የሚደርሰውን ተፅዕኖ ለመቋቋም ከፍተኛ ድርሻ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡

አያይዘውም በከተማውም ከ2 ነጥብ 7 ሚሊየን በላይ ችግኞች እንደሚተከሉም አሳውቀዋል፡፡

በአስጨናቂ ጉዱ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.