ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ከተለያዩ የስፖርት ቤተሰብ አባላት ጋር ችግኝ ተከሉ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከተለያዩ የስፖርት ቤተሰብ አባላት ጋር ችግኝ ተከሉ::
በቦሌ ክፍለ ከተማ ሲ ኤም ሲ አካባቢ በሚገኝ የስፖርት ማእከል በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ ታዋቂ አትሌቶች ፣ የወንድና ሴት የእግር ኳስ ተጫዋቾችና አሰልጣኞች እና የእግር ኳስ ደጋፊ ማህበራት ተሳታፊ ሆነዋል፡
የስፖርት ቤተሰቡ ከምክትል ከንቲባው ጋር ያደረጉት የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አለም አቀፍ ወረርሽኝ የሆነውን ኮቪድ 19 በመከላከል ዜጎች ባሉበትና በሚኖሩበት አካባቢ ችግኝ እንዲተክሉና የተከሉትንም እንዲንከባከቡ ለማነሳሳት ነው ተብሏል፡፡
የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር የሚተከሉ ችግኞች የአዲስ አበባ ከተማን ዉብ እና አረንጓዴ ከማድረግ ባለፈ የነዋሪዎችን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ መሰረት የሚጥሉ እፅዋቶች ለምግብ ፍጆታ የሚውሉ የፍራፍሬ ችግኞች መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ 7 ሚሊየን ችግኝ ለመትከል እቅድ ተይዞ እየተሰራ እንደሚገኝ ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።