የቀጣዩ ዓመት የትምህርት ንቅናቄ ማስጀመሪያ መድረክ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2017 ትምህርት ዘመን የትምህርት ንቅናቄ ማስጀመሪያ ክልላዊ መድረክ እና የፈጠራ ሥራ ዐውደ-ርዕይ በሐዋሳ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
“በሣይንስና ቴክኖሎጂ የታከለ ትውልድ ለሀገራችን ብልፅግና” በሚል መሪ ሐሳብ በተከፈተው ዐውደ-ርዕይ ላይ÷ ከክልሉ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ተማሪዎችና የክልሉ ወጣቶች የፈጠራ ሥራቸውን አቅርበዋል።
የሲዳማ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ደስታ ሌዳሞን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ ተጋባዥ እንግዶች፣ የመምህራን ማኅበር ተወካዮችና ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት በመድረኩ ተገኝተዋል፡፡
በመቅደስ አስፋው እና ደብሪቱ በዛብህ