Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 129 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ2 ሰው ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 10 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰአታት ለ5 ሺህ 274 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 129 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

ቫይረሱ ከተገኘባቸው መካከል 79 ወንድ እና 50 ሴቶች ሲሆኑ፥ ከ1 እስከ 70 አመት የእድሜ ክልል የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ናቸው።

ከዚህ ውስጥ 85 አዲስ አበባ፣ 11 ከትግራይ ክልል፣ 10 ከሶማሌ ክልል፣ 7 ከደቡብ ክልል፣ 6 ከአማራ ክልል፣ 5 ከኦሮሚያ ክልል፣ 4 ከድሬዳዋ እንዲሁም 1 ከአፋር ክልል ናቸው።

በተያያዘም በትናንትናው እለት 2 ሰዎች በቫይረሱ ሳቢያ (ከአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ) ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን፥ ይህም በቫይረሱ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎችን ቁጥር 63 አድርሶታል።

በሌላ በኩል 111 ሰዎች ከቫይረሱ ማገገማቸው ታውቋል፤ አሁን ላይም በአጠቃላይ 849 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል።

እስካሁን በኢትዮጵያ ለ197 ሺህ 361 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 3 ሺህ 759 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.