Fana: At a Speed of Life!

ግብጽ የህዳሴ ግድብ ግንባታን ለማደናቀፍ በምታደርገው ጥረት ከኢትዮጵያ ጋር ወዳጅነቷን ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያውያንንም እምነት እያጣችበት መሆኑ ተነገረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ግብጽ የህዳሴ ግድብ ግንባታን ለማደናቀፍ በምታደርገው ጥረት ከኢትዮጵያ ጋር ወዳጅነቷን ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያውያንንም እምነት እያጣችበት መሆኑ ተነገረ

የአባይን ውሀ ለብቻዬ ማለት የግብጽ የቆየ አቋም ነው።

ሀገሪቱ በአባይ ውሀ ላይ ፍላጎቷን በኢትዮጵያ ላይ ለመጫን እየታተረች ትገኛለችም።
ለዚህም የማትፈነቅለው ድጋይ የማትረግጠው ደጅ እንደማይኖር ከዳግም ድርድሩ በኋላ የምታሳየው አቋም እያሳየ ይገኛል።

የፖለቲካል ሳይንስ ምሁሩ ዶክተር ዳርእስከዳር ታየ ግብጽ በሉአላዊት ሀገር ላይ ማድረግ የማይቻለውን ድርጊት ነው እንዲፈጸምላት እየጣረች የሚገኘው ይላሉ።

የተለያዩ መጽሀፍት ጸሀፊና በአባይ ጉዳይ ላይ የረጅም ጊዜ ዳሰሳ በማድረግ የሀያሉ ሴራ በኢትዮጵያ በሚለው መጸሀፋ ላይ የግብጽን የትላንት የዛሬና የነገውን ሴራ ያጋለጡት ጸሀፊ ታደሰ ከበደም የግብጽ አካሄድ ከአለም አቀፍ ህጉም ያፈነገጠ ነው ብለዋል።

ከዚህ እውነት የራቀችው ግብጽ እዚህ ትደራደራለች እዛ የሀገራትና የተቋማት ደጅ ትማጸናለች አለፍ ሲልም የጦርነት ፕሮፖጋንዳዋን ትነዛለች ሲሉ ነው ዶክተር ዳርእስከዳር የገለፁት።

የውሀ አመጪዋ ሀገረ ኢትዮጵያ በጋራ እንጠቀም ባለች የሚገባትን አይደለም ከግብጽ እያገኘች ያለቸው።

ዶክተር ዳርእስከዳር በዚህም ግብጽ ከኢትዮጵያውያን ጋር ግንኙነቷን ብቻ ሳይሆን እምነቷንም እያጣች መጥታለች ነው ያሉት።

ኢትዮጵያ አሁን አደለም በቀጣይም ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን አስቀድማ እንደምትቀጥል አቋማን ታንጸባርቃለች ግብጽም ፍላጎቷን እያሰፋች ግድቡን ለማደናቀፍ እንደምትቀጥል ነው የተገለፀው።

ብዙ ማማተሯን የቀጠለችው ግብጽ ጦርነትም እንደ አማራጭ ማስቀመጧ ይገለፃል።
ዶክተር ዳርእስከዳር ዲፕሎማሲ እና ጦርነት ግን አብረው የሚሄዱ አይደሉም ሲሉ ገልፀዋል።

ግብጽ ተጽእኖ ለመፍጠር መቀጠሏ እንደማይቀር የሚገልፁት ምሁራኑ ኢትዮጵያም የህዳሴ ግድቡን ከመገንባትና ውሀ ከመሙላት በላይ ልታስቀድመው የምትችለው ጉዳይ ሊኖር እንደማይገባ ተናግረዋል።

ሀምሌ ወር የውሀ መሙያዋ ቀን ኢትዮጵያ ታሪኳን የምታድስበትና ጡዘቱም በአንጻራዊ አቅጣጫውን የሚቀይርበት እንሚሆንም ዶክተር ዳርእስከዳር ጠቁመዋል።

ከሀምሌ ወር የውሀ መሙላት መርሀ ግብር በኋላ ኢትዮጵያ የግብጽን ፍላጎት ተሸካሚ የሚለው ሀሳብ እንደማይኖርም ተገልጿል።

ይህም በውሀ ጉዳይ ላይ የሀገሪቱን የዲፕሎማሲ አቅም ከፍ ያደርገዋል ነው የተባለው።
ለዚህም መንግስትም ሆነ ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ አንድነቱን በማጠናከር የማይቀረውን እውነት ለማየት የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚገባቸው ተነግሯል።

በሀይለየሱስ ስዩም

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.