ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ ሌተናል ጀኔራል መሐመድ ሃምዳን ዳልጎ ጋር ተገናኙ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ ሌተናል ጀኔራል መሐመድ ሃምዳን ዳልጎ ጋር ተገናኙ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሌፍተናንት ጀነራል መሐመድ ሐምዳን ዳልጎ እንኳን ወደ ኢትዮጵያ በደህና መጡ ሲሉ በፌስቡክ ገፃቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።
ሌተናል ጀኔራል መሐመድ ሃምዳን ደጋሎ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለመምከር ዛሬ አዲስ አበባ መግባታቸው የሚታወስ ነው።
ምክትል ሰብሳቢው አዲስ አበባ ሲገቡ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸውና በጀኔራል አደም መሐመድ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።