Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች አዲስ አበባን ዓለም አቀፍ የስበት ማዕከል ለማድረግ በትጋት እየተሠራ ነው አሉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ አበባ ከተማን እንደስሟ ውብ በማድረግ ዓለም አቀፍ የስበት ማዕከል እንድትሆን እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸው ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ ከአራት ኪሎ- ቀበና እስከ ኬንያ ኤምባሲ ያለውን መንገድ በኮሪደር ልማት ሥራ አስውበን ለነዋሪዎች አገልግሎት እንዲውል ክፍት አድርገናል ብለዋል፡፡

አዲስ አበባን እንደስሟ ውብ አበባ እና ለመኖር ምቹ ከተማ በማድረግ ዓለም አቀፍ የስበት ማዕከልና የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ የገባነውን ቃል በተግባር እያሳየን ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡

በዚህም ምቹ የእግረኛ መንገዶች፣ የሞተር አልባ (ብስክሌት) መንገዶች፣ ምቹ የታክሲና አውቶቡስ ተሳፋሪዎች መጫኛና ማውረጃዎች፣ የመኪና ማቆሚያዎች፣ አረንጓዴ ቦታዎች፣ የመንገድ ዳር ማረፊያ መቀመጫዎች፣ የሕዝብ መናፈሻዎች፣ የከተማዋን ደረጃ የሚመጥኑ መብራቶችና ፏፏቴዎችን ገንብተናል ሲሉ አብራርተዋል፡፡

አዲስ አበባን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ የሆነች ዘመናዊ ከተማ የማድረግ ሥራችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉም አረጋግጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.