የኦሮሚያ ክልል ከተሞች የሕዝቡን ጥያቄ መሰረት ያደረገ ልማት እንዲኖራቸው እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የክልሉ ከተሞች የሕዝቡን የመልማት ጥያቄ መሰረት ያደረጉና ደረጃቸውን የጠበቁ መሰረተ ልማቶች እንዲኖራቸው የክልሉ መንግሥት እየሰራ መሆኑን የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማን ገለጹ።
በሞጆ ከተማ ከ360 ሚሊየን ብር በሚልቅ ወጪ የተገነቡ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የልማት ፕሮጀክቶች ዛሬ ለአገልግሎት ክፍት መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
አፈ ጉባኤዋ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር÷ የከተሞች ዕድገትና ውበት የሚረጋገጠው በመሰረተ ልማት ዝርጋታና በሚያመነጩት ገቢ በመሆኑ ሞጆም የጀመረችውን የልማት ስራ አጠናክራ እንድትቀጥል አሳስበዋል፡፡
የክልሉ ከተሞች የህዝቡን የመልማት ጥያቄ መሰረት ያደረጉና ደረጃቸውን የጠበቁ መሰረተ ልማት እንዲኖራቸው የክልሉ መንግስት በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡