የሲዳማ ክልል ከ23 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ በጀት አጸደቀ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ምክር ቤት የክልሉን የ2017 ዕቅድ ማስፈፀሚያ በጀት 23 ቢሊየን 487 ሚሊየን 368 ሺሀሰ 808.51 ብር በማድረግ በሙሉ ድምጽ አፅድቋል፡፡
የክልሉ የበጀቱ ምንጭ ከክልሉ የውስጥ ገቢ፣ ከፌዴራል መንግስት ከሚሰጥ ድጎማ እና ከሌሎች የገቢ ምንጮች የሚገኝ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
በዚህም መሰረት ከፌደራል መንግስት የድጎማ በጀት 9 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ፣ ከክልሉ ገቢ ከ14 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በላይ እንዲሁም ከክልል ፕሮግራም፣ ተቋማትና ከሴክተሮች ከ7 ነጥብ 8 በሊዮን ብር በላይ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡
በታመነ አረጋ