የምስራቅ ዕዝ ደረጃ ሶስት ሪፈራል ሆስፒታል የጤና ባለሙያዎችን አስመረቀ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአገር መከላከያ ሠራዊት የምስራቅ ዕዝ ደረጃ ሶስት ሪፈራል ሆስፒታል በክሊኒካል ነርሲንግ ሙያ በዲፕሎማ ያስተማራቸውን 800 ተማሪዎች አስመርቋል።
በምርቃ መርሃ ግብሩ ላይ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና ሌሎች የሰራዊቱ ከፍተኛ መኮንኖች እንዲሁም የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር ተገኝተዋል።
ተመራቂዎቹ ትምህርታቸውን ለሁለት ዓመት ከስድስት ወር በንድፍ ሀሳብ እና በተግባር የተከታተሉና በደረጃ አራት በዲፕሎማ መመረቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ምስራቅ ዕዝ የደረጃ ሶስት ሪፈራል ሆስፒታል ኃላፊ ኮሎኔል ብርሃኑ ዘውዱ እንደገለፁት÷ተመራቂዎቹ ከሁሉም የመከላከያ ዕዝ የተመለመሉ የሠራዊት አባላት ናቸው።
የአገር መከላከያ ሠራዊት በጤናውም ሆነ በሌሎች የሙያ መስኮች አቅሙን እያሳደገ መሆኑን ጠቅሰው የዛሬዎቹ ተመራቂዎች የዚሁ ማሳያ ናቸው ብለዋል።