በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለማስወገድ በትኩረት እንደሚሰራ ተገለፀ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለማስወገድ በትኩረት እንደሚሰራ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ( ዶ/ር) ተናገሩ።
ሚኒስትሯ ይህንን የተናገሩት ያለ እድሜ ጋብቻና የሴት ልጅ ግርዛትን ለማስወገድ የተቋቋመውን ጥምረት ወክለው በተባበሩት መንግስታት ዋና መስሪያ ቤት በተዘጋጀው የእውቅና ሽልማት መርሃ ግብር ላይ ነው።
በመርሃ ግብሩ የኢትዮጵያ መንግስት በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለማስወገድ የወሰዳችውን የህግ፣ የፖሊሲና የፕሮግራም እርምጃዎች አብራርተዋል።
ይህ አለም አቀፍ እውቅናና ሽልማት መንግስት ለስርዓተ ፆታ እኩልነትና ሴቶችን ለማብቃት ያለውን ቁርጠኝነት የበለጠ የሚያጠናክር እንደሆንም ገልፀዋል፡፡
“በቀጣይም በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለማስወገድ ትኩረት ሰጥተን በቅንጅት እንሰራለን” ማለታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡