የሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ወቅታዊ የምርት ሂደት አበረታች መሆኑ ተገለፀ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ወቅታዊ የምርት ሂደትና አጠቃላይ እንቅስቃሴ አበረታች መሆኑን የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሰሀ ይታገሱ (ዶ/ር) ገለፁ።
ዋና ስራ አስፈፃሚው የሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክን ወቅታዊ የስራ እንቅስቃሴ እና በኢንዱስትሪ ፓርኩ የሚገኙ ኢንቨስተሮችና ኩባንያዎች ያሉበትን ወቅታዊ የምርት ሂደት ተዟዙረው ተመልክተዋል።
በጉብኝታቸውም÷ ጄፒ ቴክስታይል እና ሲልቨርስፕሪንግ የተሰኙ የሁለት ዓለም አቀፍ ኩባንያዎችን የምርት ሂደት ከተመለከቱ በኋላ ከኩባንያዎቹ ሀላፊዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡
በዛሬው እለት በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከተደረገው የመስክ ምልከታ ጎን ለጎን የኢንዱስትሪ ፓርኩ ያለፉት 11 ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማና የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር እንደኖር የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡