Fana: At a Speed of Life!

በሲዳማ ክልል ከ800 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የስፖንጅ ፋብሪካ ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ከ800 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበት በሐዋሳ ከተማ የተገነባውን ታቦር ፎም የስፖንጅ ፋብሪካ መርቀው ከፍተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በወቅቱ÷ በንሳ ዳዬ ቡና ላኪ ድርጅት በይርጋለም ኢንዱስትሪ እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ የሚበረታታ ነው ብለዋል።

በአነስተኛ ቦታ ውጤታማ ከሚያደርጉ ስራዎች መካከል አንዱ ማኑፋክቸሪንግ በመሆኑ ትኩረት በመስጠት የሚሰራበት መሆኑን ጠቁመዋል።

ታቦር ስፖንጅ ፋብሪካ የስራ ዕድል በመፍጠር እንዲሁም ለክልሉ መንግስት ከሚያስገኘው ገቢ አንፃር ጠቀሜታው የጎላ በመሆኑ የሚበረታታ ነውም ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመልክቷል።

ሌሎች ባለሀብቶችም በኢንዱስትሪ እንቅስቃሴ ላይ ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ አቶ ደስታ ሌዳሞ አሳስበዋል።

ባለሀብቱ አቶ አሰፋ ዱካሞ በበኩላቸው÷ በንሳ ዳዬ ቡና ላኪ ድርጅት ከ70 በላይ የእሸት ቡና ሳይቶች ያሉት አንጋፋ ተቋም እንደሆነ ገልፀው፤ የድርጅቱ እህት ኩባንያ የሆነው የታቦር ስፖንጅ ፋብሪካ ከ800 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደተደረገበት ገልጸዋል።

ፋብሪካው ከ150 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል እንደሚፈጥርም ተናግረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.