Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማህማት የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማህማት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቅጥር ግቢና የስራ ክፍሎችን ጎብኝቷል፡፡

አየር መንገዱ በዛሬው ዕለት የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማህማትን ተቀብሎ በክብር ማስተናገዱን ገልጿል፡፡

የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር ከነበራቸው ጉብኝት ጎን ለጎን ከአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ እና ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ጋር ፍሬያማ ውይይት አድርገዋል።

ከአፍሪካ አንድነት ድርጅት ምስረታና ስኬት ጋር ቅርብ ቁርኝት ያለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የህብረቱ መስራች የነበሩ የአፍሪካ መሪዎችን ወደተለያዩ ሀገሮች በማጓጓዝ ቁልፍ ሚና መጫወቱ ይታወሳል።

አየር መንገዱ ዛሬም አፍሪካውያንን እርስ በርስ ብሎም ከተቀረው ዓለም ጋር ይበልጥ በማስተሳሰር አይተኬ ሚናውን በትጋት እንደሚወጣ አረጋግጧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.