Fana: At a Speed of Life!

የጎርጎራ ፕሮጀክት ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል የሚገኘው እና የገበታ ለሀገር አካል የሆነው የጎርጎራ ፕሮጀክት በዛሬው እለት ተመርቋል፡፡

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የጎርጎራ ፕሮጀክት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “ገበታ ለሀገር” በሚል ይፋ ካደረጓቸው ሶስት ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ መሆኑ ይታወቃል።

የገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶች የመጀመሪያው ዙር ከአዲስ አበባ ውጪ ሶስት ቦታዎችን ከአማራ ክልል ጎርጎራ፣ ከኦሮሚያ ክልል ወንጪ እና ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ኮይሻን ለማልማት ወደ ተግባር በመግባት ፕሮጀክቶቹን እውን ማድረግ ተችሏል።

የጎርጎራ ፕሮጀክትን ግንባታ የካቲት 28 ቀን 2013 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ  (ዶ/ር) ያስጀመሩ ሲሆን፤ በወቅቱም ባደረጉት ንግግር÷ ጎርጎራ የባህርዳር እና የጎንደር የቃልኪዳን ቀለበት የትስስር ማዕከል ናት ማለታቸው ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.