Fana: At a Speed of Life!

የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ስልጣኑን ያለአግባብ የተጠቀመ የፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትና ዳኛን ከሥራ አሰናበተ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ስልጣኑን ያለአግባብ የተጠቀመ አንድ የፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትና ዳኛን ከሥራ አሰናብቷል።

የአለታ ወንዶ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት እና ዳኛ በሁለት ተመሳሳይ ጉዳዮች ተጠርጥረው በተደረገ የማጣራት ስራ ወንጀለኛ ሆነው በመገኘታቸው ከስራ መሰናበታቸውን የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ደምሴ ዱላቻ ተናግረዋል።

ለሶስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የሲዳማ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 3ኛ የሥራ ዓመት 7ኛ መደበኛ ጉባኤ ዛሬ ተጠናቋል።

በጉባኤው ማጠናቀቂያ ላይ ጥሩ አፈፃፀም ለነበራቸው አካላት ዕውቅና ተሰጥቷል።

በዚህም መሠረት የእንስሳት ልማት ቢሮ በቀዳሚነት ሲሸለም፣ የሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ በሁለተኛነት እንዲሁም የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሶስተኛነት ደረጃ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

እንዲሁም የክልሉ ፀጥታ ቢሮ ልዩ ተሸላሚ ሆኗል።

በታመነ አረጋ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.