Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ም/ቤት መደበኛ ጉባዔውን እያካሄደ ነው

 

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀምሯል፡፡

በጉባዔው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርጥላሁን ከበደ የክልሉን የ2016 በጀት አመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበው ከም/ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ምክር ቤቱ በዛሬ ውሎው የ6ኛ ዙር 3ኛ ዓመት የ2ኛ መደበኛ ጉባዔ ቃል ጉባዔን፣ የክልሉ ም/ ቤት የ2016 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርትን እና የክልሉን መንግስት የ2016 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት በማድመጥ ተወያይቶ እንደሚያጸድቅ ተጠቁሟል፡፡

ጉባዔው በሦሥት ቀናት ቆይታው የክልሉ የ2017 በጀት ረቂቅ የበጀት አዋጅን ጨምሮ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ በመወያየት ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ እንደሚጠበቅም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

እንዲሁም ምክር ቤቱ በክልሉ መንግስት የ2017 በጀት ዓመት ረቂቅ የበጀት ዕቅድ ላይ በመወያየት ረቂቅ በጀቱን ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.