Fana: At a Speed of Life!

የቻይና-አፍሪካ-ዩኒዶ የልኅቀት ማዕከል ለአገልግሎት ክፍት ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የተገነባው የቻይና፣ አፍሪካ እና የተባበሩት መንግሥታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (ዩኒዶ) የልኅቀት ማዕከል ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል፣ የቻይና ዓለም አቀፍ ልማት ትብብር ኤጀንሲ ሊቀ መንበር ሉኦ ዣኦሁይ እና የዩኒዶ ዋና ዳይሬክተር ገርድ ሙለር የሦስትዮሽ የጋራ ኢኒሼቲቭ የሆነውን ማዕከል መርቀው ከፍተዋል፡፡

ማዕከሉ በአፍሪካ ዘላቂ ዕድገትን ለማረጋገጥ፣ ግብርናን ለማሻሻል እና ክኅሎትን ለማዳበር እንደሚያገለግል መገለጹን የዩኒዶ መረጃ አመላክቷል፡፡

እንዲሁም ከአፍሪካ ኅብረት አጀንዳ 2063፣ ከኢትዮጵያ የ10 ዓመት የልማት ዕቅድ እና መሰል ስትራቴጂካዊ ማዕቀፎች ጋር የተጣጣመ የልማት ፕሮግራም እንዳለውም ተጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም ለቻይና አፍሪካ ትብብር ፎረም እና ለ2030 የዘላቂ ልማት አጀንዳ አስተዋፅዖ ያበረክታል ተብሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.