Fana: At a Speed of Life!

በትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ አሥተዳደር ጀሎ በሊና ቀበሌ ቢርካ አካባቢ ሌሊት 6፡30 ገደማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

ከሟቾች በተጨማሪም በ10 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን የድሬዳዋ አሥተዳደር ፖሊስ መረጃ አመላክቷል፡፡

አደጋው የደረሰው ከድሬዳዋ ወደ ሐረር ሰው አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ በተለምዶ “ዶልፊን” የሚባለው የሕዝብ ማመላለሻ በተቃራኒ መስመር ይጓዝ ከነበረ በተለምዶ “ሲኖትራክ” ተብሎ ከሚጠራው የደረቅ ጭነት ተሸከርካሪ ጋር በመጋጨታቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.