የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ መልቀቂያ ፈተና በተሳካ ሁኔታ እየተከናወነ ነው – ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገር አቀፍ ደረጃ የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ መልቀቂያ ፈተና በተሳካ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ(ፕ/ር) ተናገሩ።
የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ማጠናቀቂያ ፈተና በሀገር አቀፍ ደረጃ በኦንላይን እና በወረቀት እየተሰጠ ይገኛል፡፡
የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ(ፕ/ር) ፈተናው ከሚሰጥባቸው ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መካከል አንዱ በሆነው የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በመገኘት የፈተና አሰጣጡን ተመልክተዋል፡፡
ብርሃኑ ነጋ(ፕ/ር) በዚሁ ጊዜ ÷ 12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ መልቀቂያ ፈተና በመላው ሀገሪቱ በጥሩ ሁኔታ እየከናወነ መሆኑን መናገራቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡
የፈተና አሰጣጡ የተሳካ እንዲሆን ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር አስፈላጊ የሆኑ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መከናወናቸውን ጠቁመዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፍቅሬ ደሳለኝ (ፕ/ር) እንዳሉት÷ በዛሬው ዕለት በዩኒቨርሲቲው 4ሺህ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናቸውን እየወሰዱ ነው፡፡