የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የ2017 በጀት 37 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ሆኖ ፀደቀ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የ2017 በጀት ከ37 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ ሆኖ ፀድቋል።
የክልሉ ምክር ቤት እያካሄደ ባለው 6ኛ ዙር፣ 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ የ2017 ዓ.ም በቀረበው ረቂቅ በጀት ላይ ከተወያየ በኋላ ነዉ በሙሉ ድምፅ ያፀደቀው ።
የምክር ቤቱ አባላት የፀደቀው በጀት ለታለመለት አላማ እንዲዉል አሳስበዋል ።
ክልሉ በ2017 የበጀት አመት ከፀደቀው 37ነጥብ 6ቢሊየን ውስጥ 75 በመቶ የሚሆነው በውስጥ ገቢ የሚሸፈን መሆኑ ተመላክቷል።
በሌላ በኩል የክልሉ ምክር ቤት በርዕሰ መስተዳድሩ የቀረቡትን አቶ ገብረመስቀል ጫላን የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድር እና የኢንተርፕራይዝና ስራ ዕድል ፈጠራ ቢሮ ሃላፊ አድርጎ በሙሉ ድምፅ ሾሟል፡፡
በተጨማሪም አቶ ዘብዲዮስ ኤካን የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ሃላፊ አድርጎ ሾሟል፡፡
በጥላሁን ሁሴን