Fana: At a Speed of Life!

በጃፓን ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር የተመራ ልዑክ የመከላከያ ፈንጅ ማምከን ቢሮን ጎበኘ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጃፓን ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ኮሚካይ ኤሊ የተመራ ልዑክ የመከላከያ ፈንጅ ማምከን ቢሮን ጎብኝቷል።

የልዑካን ቡድኑ አባላት በጉብኝታቸው ቢሮው ከተልዕኮው አንጻር እያከናወናቸው ስላሉ ተግባራት ገለጻ ተደርጎላቸዋል።

የፈንጅ ማምከን ቢሮውን አጠቃላይ የሥራ ሁኔታ እና የስልጠና ቁሶችንም ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡

የመከላከያ ፈንጅ ማምከን ቢሮ ሃላፊ ብ/ጄ ታደሰ አመሎ÷ቢሮው በተለያዩ ጊዜያት በተደረጉ ጦርነቶች ምክንያት ተቀብረው የቀሩ ፈንጅና ተተኳሾችን የማስወገድና የማምከን ተልዕኮ እንዳለው ተናግረዋል፡፡

ቢሮው በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች እየተዘዋወረ ፈንጅና ሌሎች ተተኳሾችን እያስወገደ ቢሆንም በሥራ ሒደት የግብዓትና ሌሎች አስፈላጊ ቁሶች እጥረት እንደሚያጋጥሙት ጠቅሰዋል፡፡

በዚህ ሳቢያም ስራውን በተፈለገው ፍጥነት ማስኬድ እንዳልተቻለ ጠቁመው÷የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትና የሰብዓዊ እርዳታ ሰጪ ድርጅቶች ድጋፍ እንዲያደርጉ መጠየቃቸውን የመከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.