Fana: At a Speed of Life!

በቁሊቶ ከተማ ለሚገነባው ስታዲየም የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው በሃላባ ዞን ቁሊቶ ከተማ ለሚገነባው ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም የመሰረት ድንጋይ አስቀመጡ።

አቶ እንደሻው በዚህ ወቅት እንደገለጹት÷የስታዲየሙ መገንባት በክልሉ ብቁና ተወዳዳሪ ስፖርተኞችን በማውጣት በሀገር አቀፍ ደረጃ ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት የሚያስችል ነው።

ስታዲየሙ የግንባታ ሥራው በሦስት ምዕራፍ ተከፋፍሎ እንደሚከናወንና ከ500 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ እንደሚደረግበት ገልጸዋል።

የሃላባ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ታገል ጌታቸው በበኩላቸው÷አካባቢው ለስፖርት ዘርፍ ጥሩ ዝንባሌ ያላቸው ወጣቶችና ማህበረሰብ ያሉበት መሆኑን ተናግረዋል።

በመጀመሪያ የስታዲየሙ ግንባታ ምዕራፍ የሰው ሰራሽ ሜዳና መሰል ሥራዎች እንደሚከናወኑ መጠቀሱንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በሁለተኛውና በሦስተኛው ምዕራፍ ደግሞ የመሮጫ መም እና የመብራት እንዲሁም ሌሎች ሥራዎች እንደሚከናወኑ የተገለጸ ሲሆን÷ግንባታው በዞኑ ህዝብ ተሳትፎ እንደሚከናወን ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.