የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2016 ትምህርት ዘመን በወረቀትና በበይነ መረብ ሲሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ፡፡
በተመሳሳይ መልኩ በትግራይ ክልል እየተሰጠ ያለው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ነገ አርብ ከሰዓት በፊት እንደሚጠናቀቅ አገልግሎቱ ገልጿል፡፡
ባለድርሻ አካላት ፈተናው በስኬት እንዲጠናቀቅ ላበረከቱት አስተዋጽኦ አገልግሎቱ ምስጋና አቅርቧል፡፡