የዘንድሮ የአረንጓዴ ዓሻራ ተካፋይ እንድትሆኑ ጥርዬን አቀርባለው – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ህብረተሰቡ የዘንድሮ የአረንጓዴ ዓሻራ መርሐ ግብር ተካፋይ እንዲሆን ጥሪ አቀረቡ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች ጋር በመሆን በጫካ ፕሮጀክት ሀገር በቀል የአረንጓዴ አሻራ ችግኞችን ተክለዋል።
ይህን ተከትሎም ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው፤ “የዘንድሮ የአረንጓዴ ዓሻራ ተካፋይ እንድትሆኑ ጥርዬን አቀርባለው” ብለዋል፡፡
የባህር ዛፍን በሀገር በቀል የዛፍ ዝርያዎች የመተካቱ ሂደት ተጠናክሮ መቀጠሉንም ነው ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክተው፡፡