Fana: At a Speed of Life!

ጨፌ ኦሮሚያ መጀበኛ ጉባዔውን ነገ ማካሄድ ይጀምራል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)ለሁለት ቀናት የሚቆየው የጨፌ ኦሮሚያ 6ኛ የስራ ዘመን፣ 3ኛ ዓመት 7ኛ መደበኛ ጉባዔ ነገ በአዳማ ከተማ መካሄድ ይጀምራል።

ይህንን አስመልክቶ የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባዔ ሰዓዳ አብዱራህማን በሰጡት መግለጫ÷በጉባዔው የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውይይት ተደርጎ ውሳኔዎች ይተላለፋሉ ብለዋል።

የበጀት ዓመቱ የክልሉ መንግስት አፈፃፀም ሪፖርት እና ቀጣይ ዕቅድ ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበት ነው አፈ ጉባዔዋ የገለፁት፡፡

የበጀት ዓመቱ የስራ አፈፃፀም እንዲሁም ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ የሚመዘኑበት መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ጨፌው የሰላም እና የፀጥታ ጉዳይ፣ የልማት ስራዎች አፈፃፀም ፣ የመልካም አስተዳደር እና የአገልግሎት አሰጣጥ ቀዳሚ የውይይት ርዕሶች እንደሚሆኑም ነው አፈጉባዔዋ ያመላከቱት፡፡

በተጨማሪም ጉባዔው በሁለት ቀናት ቆይታው  ረቂቅ አዋጆችን ተወያይቶ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

 

በመራኦል ከድርና ሙሉ ዋቅሹሜ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.