Fana: At a Speed of Life!

የሆስፒታሉ ማስፋፊያ የክልሉን የሜዲካል ቱሪዝም የሚያጎለብት ነው -አቶ ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀረር ፌደራል ፖሊስ ሆስፒታል ማስፋፊያ ፕሮጀክት የክልሉን የሜዲካል ቱሪዝም ይበልጥ የሚያጎለብት ነው ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለፁ።

አቶ ኦርዲን በድሪ ከ1 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ እየተገነባ የሚገኘውን የሐረር ፌደራል ፖሊስ ሆስፒታል ማስፋፊያ ፕሮጀክት ተመልክተዋል።

በመስክ ምልከታውም እንደተገለፀው ሆስፒታሉ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስን ጨምሮ የአጎራባች ክልሎች የፖሊስ አባላት እና ቤተሰቦች እንዲሁም የአካባቢው ማህበረሰብ በቅርበት አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል ነው።

በክልሉ ለጤና ኮሪደር ልማትና የጤና አገልግሎት ተደራሽነት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ወደ ስራ መገባቱን ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል፡፡

የሆስፒታሉ ማስፋፊያ በክልሉ በጤና ዘርፍ የሚሰጠውን አገልግሎት ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ አስተዋፅኦ የሚያበረክት እንደሆነም ገልፀዋል።

ፕሮጀክቱ ጥሩ በሚባል አፈፃፀም ላይ እንደሚገኝ ገልፀው÷ በፍጥነት ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት እንዲችል የክልሉ መንግስት ድጋፍ እንደሚያደርግም መናገራቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.