Fana: At a Speed of Life!

ተጎጂዎችን መልሶ በማቋቋም ሂደት ከድሬ ዳዋ አስተዳደር ጎን እንቆማለን-አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ‘አሸዋ ገበያ’ በተከሰተው የእሳት አደጋ ምክንያት የተጎዱ ዜጎችን መልሶ በማቋቋም ሂደት ከአስተዳደሩ ጎን በመቆም ድጋፍ እንደሚያደርጉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ አስታውቀዋል።

አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፥ በድሬዳዋ ‘አሸዋ ገበያ’ የተከሰተው የእሳት አደጋ ያደረሰውን ጉዳት ተመልክተዋል፡፡

በገበያ ስፍራው ላይ በደረሰው ውድመት ማዘናቸውን የገለፁት አፈ-ጉባኤው÷ ተጎጂዎችን መልሶ በማቋቋም ሂደት ከአስተዳደሩ ጎን በመቆም ድጋፍ እንደሚያደርጉ ማስታወቃቸውን የአስተዳደሩ ከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

የድሬዳዋ ከንቲባ ከድር ጁሀር ÷በእሳት አደጋው ስለደረሰው የጉዳት መጠን እንዲሁም ተጎጂዎችን ለማቋቋም አስተዳደሩ እያከናወነ ስለሚገኘው ድጋፍ የማሰባሰብ ሂደት ለአፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ገለፃ አድርገዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.