Fana: At a Speed of Life!

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለ2017 በጀት ዓመት ከ8 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በላይ በጀት አጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት ለክልሉ የ2017 በጀት ዓመት እቅድ ማስፈጸሚያ የሚሆን ከ8 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በላይ በጀት አጽድቋል፡፡

የክልሉ ምክር ቤት ባካሄደው ጉባዔ ለ2017 በጀት ዓመት 8 ቢሊየን 974 ሚሊየን 531 ሺህ 586 ብር ያጸደቀ ሲሆን÷ከተያዘው በጀት ውስጥ 3 ቢሊየን 784 ሚሊየን 430 ሺህ 733 ብሩ ከፌዴራል መንግስት በድጎማ የሚገኝ ነው ተብሏል፡፡

4 ቢሊየን 500 ሚሊየን ብሩ በክልሉ ከሚሰበሰብ ገቢ እንደሚሸፈን እና ቀሪው ደግሞ ከተለያዩ የገቢ አማራጮች የሚገኝ መሆኑን የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ አቶ ዚያድ አብዱላሂ ገልጸዋል።

በ2017 ለክልሉ የተያዘው በጀት ካለፈው 2016 በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ6 በመቶ ጭማሪ እንዳለውም የክልሉ ኮሙኒኬሽ መረጃ ያመላክታል፡፡

የምክር ቤት አባላትም÷የህዝቡን የልማት ጥያቄዎችን በወቅቱ ለመመለስ በክልሉ ያሉትን ለገቢ የሚሆን ምቹ አቅሞች በመጠቀም የሚሰበሰበውን ገቢ እያሳደጉ መሄድ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በበጀት ዓመቱ የተያዘውን በጀት በአግባቡ ለታለመለት ዓላማ እንዲውል በየደረጃው ክትትል ማድረግ ይጠበቃልም ብለዋል።

የክልሉ ምክር ቤት በጀቱን ከመረመረ በኋላ በሙሉ ድምጽ በማጽደቅ 18ኛ መደበኛ ጉባዔውን አጠናቅቋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.