Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ወንድማማቾች መመካከሪያ መድረክን ለማካሄድ እየተዘጋጀች መሆኗ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2017 (ኤፍቢ ሲ) በአዲስ አበባ የሚካሄደውን የአፍሪካ ወንድማማቾች መመካከሪያ መድረክ ለማዘጋጀት በቂ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አስታወቁ፡፡

አቶ ተመስገን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ ባሳለፍነው ሚያዝያ ወር ከአፍሪካ ከተሞች ፎረም ብሔራዊ አስተባባሪ ዐቢይ ኮሚቴ ጋር መወያየታቸውን አስታውሰዋል፡፡

በወቅቱም በአዲስ አበባ በሚካሄደው “ዘላቂ የክትመት ምጣኔ ለአፍሪካ ትራንስፎርሜሽን – አጀንዳ 2063” ላይ መክረናል ብለዋል፡፡

በዛሬው ዕለትም ከዚሁ ዐቢይ ኮሚቴ ጋር በፎረሙ ዙሪያ እየተከናወኑ ያሉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን ገምግመናል ነው ያሉት፡፡

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ወንድማማቾች መመካከሪያ መድረክን በአግባቡ ለማዘጋጀት የሚያስችላትን በቂ ቅድመ ዝግጅት እያደረገች እንደምትገኝም በግምገማችን አይተናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.