በአዲስ አበባ በትራፊክ አደጋ የ3 ሰዎች ሕይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ ንጋት 11 ሠዓት ከ14 ላይ በንፋስ-ስልክ ላፍቶ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 14 ሰፈራ አካባቢ በተከሰተ የትራፊክ አደጋ የሦስት ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ አራት ሰዎች ከባድ የአካል ጉዳት ደረሰባቸው፡፡
አደጋው የተከሰተው ሰባት ሰዎችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ደብል ፒክ አፕ ተሽከርካሪ ከቆመ ከባድ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ መሆኑን የእሳት አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
በዚህም በተሽከርካሪው ተሳፍረው ከነበሩ ሰባት ሰዎች መካከል ሦስቱ ወዲያውኑ ሕይወታቸው ሲያልፍ ቀሪ አራት ሰዎች ከባድ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው እና የሕክምና ዕርዳታ እያገኙ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በሌላ በኩል ትናንት ምሽት 4 ሠዓት ከ43 ላይ በንፋስ-ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 አደይ አበባ አካባቢ በሚገኝ DN የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ላይ በአጋጠመ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡