Fana: At a Speed of Life!

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችን አጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት በርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን የቀረቡ የካቢኔ አባላትን ሹመት አጽድቋል፡፡

በዚህም አቶ ባበክር ኻሊፋ የግብርና ቢሮ ኃላፊ፣ ተመስገን ዲሳሳ (ዶ/ር) የትምህርት ቢሮ ኃላፊ፣ ወ/ሮ አለምነሽ ይባስ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ፣ አቶ ዚያድ አብዱላሂ የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል፡፡

እንዲሁም አቶ መሐመድ አልማሂ የከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ፣ አቶ ተፈሪ አበበ የገቢዎች ቢሮ ቢሮ ኃላፊ፣ ወ/ሮ ሀጂራ ኢብራሂም የውኃና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ፣ አቶ ወልተጂ በጋሎ የጤና ቢሮ ኃላፊ፣ አቶ አስር ኢብራሂም የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ፣ ወ/ሪት ምስኪያ አብደላ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሆነው ሹመታቸው በምክር ቤቱ መጽደቁን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በተጨማሪም አቶ አድማሱ ሞርካን የማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ፣ አቶ ካሚል ሀሚድ የመሬትና የህብረት ሥራ ማኅበራት ቢሮ ኃላፊ፣ አወቀ አይሸሽም (ዶ/ር) የመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ፣ አቶ አብዱሠላም ሸንገል የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ፣ አቶ አመንቴ ገሺ የኢንቨስትመንትና ኢንዱስተሪ ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል።

እንዲሁም አቶ ቢንያም መንገሻ የሠላምና ግንባታና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ፣ አቶ መሐመድ ሀሚድ የፍትህ ቢሮ ኃላፊ፣ አቶ መለሰ በየነ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ፣ ቃሲም ኢብራሂም የፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው በምክር ቤቱ የተሾሙ ሲሆን ቃለ-መሐላ ፈጽመዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.