በተወሰኑ ዕቃዎች ላይ የተጣለው የባንክ የውጭ ምንዛሪ ገደብ ተሻረ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሙሉ በሙሉ በነዳጅ የሚሰሩ በታሪፍ መፅሐፉ አንቀፅ 87.03 የሚመደቡ ሙሉ በሙሉ ተገጣጥመው የቀረቡ የቤት አውቶሞቢል እና ባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ላይ የተጣለው እገዳ እንደተጠበቀ ሆኖ በተቀሩት ዕቃዎች ላይ የተጣለው የውጭ ምንዛሪ ገደብ ውሳኔ ከነማሻሻያው መሻሩ ተገለፀ፡፡
መንግስት በቁጥር ክሂገ 1/7/252 በቀን 04/02/2015 በተላለፈ ውሳኔ እና በቁጥር ታፖመ/ፖ/29/16 በቀን 28/6/2016 በተሻሻለው በተወሰኑ ዕቃዎች ላይ የባንክ የውጭ ምንዛሪ ገደብ እንዲጣል ማድረጉ ይታወሳል፡፡
ስለሆነም ሙሉ በሙሉ በነዳጅ የሚሰሩ በታሪፍ መፅሐፉ አንቀፅ 87.03 የሚመደቡ ሙሉ በሙሉ ተገጣጥመው የቀረቡ የቤት አውቶሞቢል እና ባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ላይ የተጣለው እገዳ እንደተጠበቀ ሆኖ በተቀሩት ዕቃዎች ላይ የተጣለው የውጭ ምንዛሪ ገደብ ውሳኔ ከነማሻሻያው ከሐምሌ 21 ቀን 2016ዓ.ም ጀምሮ የተሻረ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር ገልጿል፡፡