Fana: At a Speed of Life!

ድሚትሪ ሜድቬዴቭ በጎፋ ዞን በደረሰው አደጋ የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገለፁ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዩናይትድ ሩሲያ ፓርቲ ሊቀመንበር ድሚትሪ ሜድቬዴቭ በጎፋ ዞን በደረሰው አደጋ የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገልጸዋል።
ባስተላለፉት የሐዘን መግለጫም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተው የተፈጥሮ አደጋ ሰዎች መሞታቸውን በመስማቴ ጥልቅ ሐዘን ተሰምቶኛል ብለዋል።
ሕይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች መጽናናትን የተመኙ ሲሆን÷ ለተጎዱትም ቶሎ እንዲያገግሙ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.