በመላው ዓለም የስደተኞች ቀን እየተከበረ ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 13 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የኢ. ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ዛሬ በመላው ዓለም የስደተኞች ቀን እየተከበረ መሆኑን ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስ ቡክ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክታቸው÷”ዛሬ በመላው ዓለም የስደተኞች ቀን እየተከበረ ይገኛል፣ ኢትዮጵያም መኖሪያቸው ላደረጓት ሁሉ ሰላማዊ መጠጊያ ሆና ትቀጥላለች።”ብለዋል።
በ2011 የነበረንን የስደተኛ ሕግ በማሻሻል፣ ስደተኞች የባንክ አገልግሎት፣ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት እና የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባን አካትቶ፣ ተጨማሪ መብቶች እንዲኖሯቸው ተደርጓልም ነው ያሉት ዶክተር ዐቢይ ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከ900 ሺህ ለሚበልጡ እና በ27 ጣቢያዎች ለሚገኙ ስደተኞች ዕለታዊ ፍላጎትን የማሟላት ሥራ እየተከወነ መሆኑን ጠቁመው÷ከዚያ ጎን ለጎንም ዘላቂ መፍትሔዎች ይዘጋጃሉ ብለዋል፡፡
አያይዘውም ”ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የጋራ አመራርን በመጠቀም ከቀዬ እና ከሀገር የመፈናቀያ ዋነኛ መንሥኤዎችን ለማስወገድ እንዲሠራ ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡”ብለዋል