Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ ክልል የባለድርሻ አካላት የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል የባለድርሻ አካላት የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ እየተካሄደ ነው።

የባለድርሻ አካላቱ የፖለቲካ ፓርቲ፣ ሶስቱ የመንግስት አካላት፣ ማህበራትና ተቋማት፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰዎችና ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተመረጡ 60 ተወካዮች ናቸው።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር መላኩ ወልደማርያም እንደተናገሩት÷ ከባለድርሻ አካላት የምክክር ምዕራፍ ለክልሉም ሆነ ለሀገር የሚጠቅሙ እንዲሁም መግባባት ላይ የሚያደርሱ ሀሳቦችና አጀንዳዎች ይጠበቃሉ።

ተወካዮቹ በአጀንዳ ማሰባሰብና ልየታ ሂደቱ ላይ ጥሩ አስተዋጽኦ ለማድረግና መግባባት ላይ ለመድረስ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉም ጠይቀዋል።

ሰላምን በማረጋገጥ ልማትን በማምጣት ለትውልድ የሚሻገር ስራ ለመስራት በዚህ የምክክር ምዕራፍ የሚዋጣው ሀሳብ ወሳኝነት እንዳለውም አስገንዝበዋል።

ምክክሩ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ.ም የሚቀጥል ሲሆን÷ ባለድርሻዎች አጀንዳዎቻቸውን ለይተውና አደራጅተው ለኮሚሽኑ ያስረክባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በዓለምሰገድ አሳዬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.