Fana: At a Speed of Life!

ከ21 የአፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ የጤናና የፋይናንስ አመራሮች የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ21 የምስራቅና ደቡብ አፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ የጤና እና የፋይናንስ አመራሮችና ባለሙያዎች የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል፡፡

የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ እና የጤና ሚኒስትር ዴዔታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ አመራሮችና ባለሙያዎችን የዓድዋ ድል መታሰቢያን አስጎብኝተዋል፡፡

ጎብኚዎቹ የጥቁር ህዝቦች እውነተኛ ተጋድሎና የድል ብስራት ምን ይመስል እንደነበር የሚያመላክቱ የቅርስ ስብስቦች በዓድዋ ድል መታሰቢያ ተደራጅተው መቅረባቸው የኢትዮጵያን የእድገት ጉዞ አሳይቶናል ብለዋል።

የዓለም የምግብ ፕሮግራም (ዩኤንኤፍፒ) እና የዓለም ጤና ድርጅት ጎብኚዎች በበኩላቸው÷ የሰው ዘር መገኛ በሆነችው ኢትዮጵያ ተገኝተው ታሪካዊ ቦታውን በመጎብኘታቸው መደሰታቸውን ገልፀዋል።

የዓድዋ ድል መታሰቢያን ከጎበኙ በኋላ በሰጡት አስተያየት በአዲስ አበባ ከተማ ሁለንተናዊ ለውጥ መደመማቸውን አንስተዋል፡፡

ኢትዮጵያ ነጻነቷን አስከብራ ለጥቁር ሕዝቦች የነጻነት ተምሳሌት እንደሆነች ሁሉ በልማቱም የአፍሪካ ምሳሌ መሆኗ የማይቀር እንደሆነ መግለጻቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

አፍሪካውያን የኩራት ምንጭ የሆኑ ታሪካዊ ስኬቶችን የሚዘክር የሥራ ውጤት ማየት በመቻላቸው መደሰታቸውንም ጠቅሰዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.