ለወጣቱ የክህሎት መር ስራ ዕድል መፍጠር ላይ በልዩ ትኩረት ሊሰራ ይገባል – አቶ ጥላሁን ከበደ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፀጋዎቻችንን በመለየት ለወጣቱ የክህሎት መር ስራ ዕድል መፍጠር ላይ በልዩ ትኩረት ሊሰራ ይገባል ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርእሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ተናገሩ፡፡
የክልሉ ስራ እድል ፈጠራ እና ኢንተርፕራይዝ ቢሮ በ2016 ዓ.ም የታዩ ጉድለቶችን በማረም በ2017 ዓ.ም የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ የሚያስችል መድረክ በአርባምንጭ ከተማ እያካሄደ ነው፡፡
የቢሮው ኃላፊ አቶ ገብረመስቀል ጫላ÷ ዘርፉ በሀገር እድገት ላይ የሚጫወተው ሚና ትልቅ ከመሆኑ አንጻር ባለፈው አመት በታየው ጉድለት ላይ ትኩረት ሰጥተን ልንሰራ ይገባል ብለዋል።
ሀገር የዜጎች ድምር ውጤት እንደመሆኑ ወጣቶችን ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ወደ ስራ በማሰማራት ኢኮኖሚያቸው አድጎ ማየት እስክንችል ድረስ መስራት አለብን ብለዋል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥለሁን ከበደ በበኩላቸዉ÷ ፀጋዎቻችንን በመለየት ለወጣቱ የክህሎት መር ስራ ዕድል መፍጠር ላይ በልዩ ትኩረት ሊሰራ ይገባል ነው ያሉት፡፡
ለዜጎች የስራ እድልን መፍጠር እያደጉ ላሉ ሀገራት ወሳኝ ነው ያሉ ሲሆን÷ በ2017 ዓ.ም ሁሉም ልዩ ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡
በጌትነት ጃርሳ