ስፔን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ጥላው የነበረውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አነሳች
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 15 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ስፔን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ጥላው የነበረውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አነሳች።
ሃገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በማንሳት ድንበሯን ለአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት ክፍት አድርጋለች።
ይህን ተከትሎም ስፔናውያን ለወራት ተለይተዋቸው የቆዩ ወዳጅ ዘመዶቻቸውን እየጠየቁ ነው።
ከዚህ ባለፈም ከፖርቹጋልና ብሪታንያ ውጭ ያሉ የተለያዩ ሃገራት ዜጎች ወደ ስፔን መግባት ጀምረዋል።
መንገደኞች ስፔን ሲገቡ የአፍ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግና በሚንቀሳቀሱበት ወቅት የሙቀት ልዬታ ይደረግላቸዋል።
በተጨማሪም ስፔን ከገቡ በኋላ የሚያርፉበትን ቦታ የማሳወቅ ግዴታም አለባቸው።
ምንጭ፡- አልጀዚራ