Fana: At a Speed of Life!

ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ በድሬዳዋ አስተዳደር የልማት ሥራዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ የተለያዩ ክልሎች ርዕሰ መሥተዳድሮች በድሬዳዋ አሥተዳደር የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝታቸውም÷ የመንገድ መሠረተ ልማቶችን ጨምሮ የሌማት ትሩፋት ሥራዎችን እና የድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጣናን እንዲሁም የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድን አገልግሎቶችን ተመልክተዋል፡፡

በነጻ የንግድ ቀጣናው ያለውን የስራ እንቅስቃሴና አሁናዊ አቅም በተመለከተም ገለጻ ተደርጓል።

በተጨማሪም የሰቆጣ ቃል ኪዳን ትግበራና ሥርዓተ-ምግብ ከሕብረተሰብ ጤና አገልግሎት ጋር ተቀናጅተው ተግባራዊ እየተደረጉ በሚገኙበት ቢዮ አዋሌ ቀበሌን ተሞክሮ የጎበኙ ሲሆን÷ ከትግበራው ተጠቃሚዎች ጋርም ተወያይተዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በከተማ ግብርና እና የሌማት ትሩፋትም በቂ የወተት፣ የእንቁላልና የማር ውጤቶችን በማምረት የመቀንጨር ችግርን ለመቅረፍ የሚያስችል እና ገበያውን የሚያረጋጉ ሥራዎችን ተመልክተናል ብለዋል።

ኢትዮጵያን የነፃ ንግድ ቀጣና በማምረቻ ኢንዱስትሪ እንዲሁም በገቢና ወጭ ንግድ ማዕከል ከማድረግ ባሻገር ለወጪ ንግድ ብቻ ሳይሆን ተኪ ምርት ላይም ትልቅ አስተዋፅዖ የሚያበረክት መሆኑን ገልጸዋል።

በፍሬሕይወት ሰፊው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.