አየር መንገዱ ለሼባ ማይልስ ሲልቨር ደንበኞች የመዝናኛ አገልግሎት የሚሰጥ ላውንጅ አስመረቀ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሼባ ማይልስ ሲልቨር ደንበኞች የተለያዩ የመዝናኛ እና ማረፊያ አገልግሎት የሚሰጥ የሲልቨር ላውንጅ አስመርቆ ለአገልግሎት ክፍት አድርጓል፡፡
ላውንጁ የተከፈተው በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ መሆኑን የአየር መንገዱ መረጃ ያመላክታል፡፡
ላውንጁ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሼባ ማይልስ ሲልቨር ደንበኞች መንፈስን የሚያድሱና እና ዘና የሚያደርጉ አገልግሎቶች የሚያገኙበት ስፍራ ነው ተብሏል፡፡