አቶ እንዳሻው ጣሰው እና ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የወራቤ ንጹሕ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክትን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው እና የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የወራቤ ንጹህ መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክትን ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝቱ ወቅት የፕሮጀክቱ ተቋራጭ ÷ፕሮጀክቱ 80 ኪሎ ሜትር የመስመር ዝርጋታ እንደሚኖረው እና 60 ሺህ ሰዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት የፕሮጀክቱ ኤሌክትሮ ሜካኒካል እቃዎች በመግባት ላይ መሆናቸውን ጠቁመው÷ የመብራት ተከላ ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝም ጠቅሰዋል፡፡
የፕሮጀክቱ የውሃ ጉድጓዶች እስከ 20 ዓመት አገልግሎት መስጠት እንደሚችሉ ነው የተመላከተው፡፡
የፕሮጀክቱን ግንባታ በ1 ዓመት ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ እንደሚሰራም የፕሮጀክቱ ተቋራጭ ገልጸዋል፡፡
በኤርሚያስ ቦጋለ