Fana: At a Speed of Life!

የሕብረተሰብ ጤና የ3ኛ ዲግሪ ትምህርት በ2 ዩኒቨርሲቲዎች ሊጀመር ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕብረተሰብ ጤና የሶስተኛ ዲግሪ የትምህርት መርሃ ግብር በሁለት ዩኒቨርሲቲዎች ሊጀመር መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በሚኒስቴሩ የሰው ሃብት ልማትና ማሻሻያ መሪ ስራ አስፈፃሚ አሰግድ ሳሙኤል÷ በጤናው ዘርፍ በሁሉም መስኮች የሞያተኞችን ቁጥር ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህ ረገድ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የተለያዩ ተግባራት እየተከነወኑ መሆኑን ጠቅሰው÷ እስከ 2024 የሚያገለግል የጤና የሰው ሃይል ስትራቴጂ ክለሳ ተደርጓል ብለዋል።

በተያዘው በጀት አመትም በተጠናከረ መልኩ የሚቀጥል መሆኑን አረጋግጠው÷ የሕብረተሰብ ጤና ትምህርት በሶስተኛ ዲግሪ (ዶክተር ኦፍ ፐበሊክ ኸልዝ) በሀረማያ እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲዎች ለመጀመር ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል።

በእስካሁኑ ሂደት የስርዓተ ትምህርት ዝግጅት መጠናቀቁን እና በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ የሚቀበል ሲሆን በቀጣይ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ይጀመራል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የሰውሰራሽ የአካል ድጋፍ ባለሙያዎች ትምህርት በመጀመሪያ ዲግሪ ደረጃ ለመጀመር ዝግጅት መጠናቀቁንም ገልጸዋል።

የኩላሊትና ካንሰር ህክምና የሚሰጡ እንዲሁም የኤሌክትሮኒክስ ሜዲካል ምዝገባ ስራውን የሚያግዙ የዲጂታል ጤናውን የሚያግዙ ባለሙያዎችን ለማሰልጠን ይሰራልም ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.