አቶ ሽመልስ አብዲሳ በምስራቅ ሐረርጌ ዞን በክላስተር የለማ ስንዴ ማሳን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ የተመራ ልዑክ በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ጭናክሰን ወረዳ በክላስተር የለማ ስንዴ ማሳን ጎብኝቷል።
በወረዳው በክረምት እርሻ በ2 ሺህ 800 ሔክታር መሬት ላይ በክላስተር የተዘራ ስንዴ እየለማ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡
በሌላ በኩል ልዑካኑ በወረዳው በ500 ሚሊየን ብር ወጪ እየተከናወነ የሚገኘውን የመረር ፊና መስኖ ፕሮጀክት ግንባታ መመልከታቸውን የዞኑ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡