የከተማ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ተቆጣጣሪ አካል ማቋቋሚያ ሕጋዊ ማዕቀፍ ላይ ምክክር እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በተዘጋጀው የከተማ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን አገልግሎት ተቆጣጣሪ ማቋቋሚያ ሕጋዊ ማዕቀፍ ላይ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር )÷ ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ የሚታዩ ከአስተዳደር፣ የራስን የጥገናና ሌሎች አቅሞች ከመገንባት፣ተደራሽ ከመሆንና ውጤታማነትን ከማሳደግ አንጻር አስቻይ ተቋምና ሕጋዊ ማዕቀፍ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።
የከተማ ውሃና ሳኒቴሽን አገልግሎት ላይ የግንዛቤ ፈጠራ ሥራዎች ትኩረት ሊደረግባቸው እንደሚገባም አንስተዋል።
በመድረኩ የትምህርት ሚኒስትር ዴዔታ አየለች እሸቴን ጨምሮ ሌሎች ከሀገር ውስጥና ከአፍሪካ ሀገራት የተጋበዙ እንግዶች መገኘታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል