Fana: At a Speed of Life!

የክልሉ ሕዝብ በአንድ ጀምበር በሚከናወነው ችግኝ ተከላ በንቃት እንዲሳተፍ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል ሕዝብ ነሐሴ 17 ቀን 2016 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ በአንድ ጀምበር በሚካሄደው አረንጓዴ ዐሻራ የማኖር መርሐ-ግብር በንቃት እንዲሳተፍ የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ ጥሪ አቀረቡ፡፡

አረንጓዴ ዐሻራ የምግብ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ከድህነትና ተረጂነት ለመውጣት የሚደረገውን ጥረት የሚያጠናክርና ሁለንተናዊ ጠቀሜታ ያለው መሆኑንም አቶ ኦርዲን አስገንዝበዋል፡፡

በመሆኑም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአንድ ጀምበር 600 ሚሊየን ችግኝ ለመትከል ያቀረቡትን ጥሪ ተከትሎ ክልሉ አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቅቋል ብለዋል፡፡

የክልሉ ሕዝብም የፊታችን ዓርብ በአንድ ጀምበር በሚካሄደው ችግኝ ተከላ በነቂስ በመውጣት እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.