Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ ከሚኒስትሮች እና ሚኒስትር ዲኤታዎች ጋር በእንጦጦ አረንጓዴ ዐሻራን አሳረፉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር  ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከሚኒስትሮች እና ሚኒስትር ዲኤታዎች ጋር  ዛሬ በእንጦጦ አረንጓዴ ዐሻራን አሳርፈዋል።

ዶክተር ዐቢይ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት ÷በአካል ተራርቀን፤ ንጽሕና ጠብቀን፣ እርስ በርስ ተረዳድተን- ኢትዮጵያን ከኮሮና እንታደግ  ብለዋል።

አገር አቀፉ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ግንቦት 28 ቀን 2012 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በሀዋሳ ከክልል እና ፌደራል መንግስታት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም ከአካባቢው ሀገር ሽማግሌዎችጋር በመሆን በጋራ በታቦር ተራራ ላይ ማስጀመራቸው ይታወሳል።

በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በሀገር አቀፍ ደረጃ 5 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል እቅድ ተይዟል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.