Fana: At a Speed of Life!

በቱሪዝም ዘርፍ ኢንቨስት ለሚያደርጉ አካላት ማበረታቻ እንደሚደረግ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ በቱሪዝም ዘርፍ ኢንቨስት ማድረግ ለሚፈልጉ አካላት የተለያዩ ማበረታቻዎች እንደሚደረጉ ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የቱሪዝም ሚኒስትር ዴዔታ ስለሺ ግርማ ከቻይና-ሽያንዥ ከመጣ የልዑካን ቡድን ጋር በቱሪዝም ኢንቨስትመንት ዘርፍ ላይ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ሚኒስትር ዴዔታው ለልዑኩ አባላት ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የቱሪዝምና ኢንቨስትመንት አመራጮችን አብራርተዋል፡፡

በቱሪዝም ዘርፍ ኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ያልተነካ የቢዝነስ አማራጭ መኖሩንም አስረድተዋል፡፡

መንግሥት በቱሪዝም ዘርፍ ኢንቨስትመንት ለሚሳተፉ ባለሃብቶች ለማበረታቻ የሚሆን የመሬት አቅርቦትን ጨምሮ ከቀረጥ ነጻ የሆነ ለሥራ የሚውል የግንባታ ግብዓት እንደሚፈቅድ ገልጸዋል፡፡

ኢንቨስተሮች በቱሪዝም ዘርፍ፣ በመሰረተ-ልማት ግንባታ፣ በሆቴል፣ በሎጅ እና በቱሪዝም ትምህርት ቤት መሳተፍ ይችላሉ ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

ኢትዮጵያ በቱሪዝም ዘርፍ በተለያዩ ሙያዎች የሰለጠነ በቂ የሰው ኃይል እንዳላት ጠቅሰው÷ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በበርካታ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች የሚበር መሆኑም ለቱሪስቶች ተጨማሪ ምቾት ነው ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.