Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የአደጋ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓት መዘርጋቱን የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ የአደጋ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓት መዘርጋቱን የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ።

የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያ ካሚል፥ የቅድመ ማስጠንቀቂያ እና ፈጣን ምላሽ ስርዓት አካል የሆነው የቅድመ ማስጠንቀቂያ ፕሮጀክት በይፋ ወደ ስራ ሊገባ እንደሆነ በትናንትናው እለት ገልፀዋል።

ስርዓቱ ከፍተኛ አደጋ አድራሽ የሆኑ የአየር ንብረት ለውጥ፣ ሰደድ እሳት፣ ጎርፍ እና ሌሎች የደህንነት ችግሮች በሚከሰትባቸው ወቅት በአደጋው የሚጎዱ ወይም ሊጎዱ የሚችሉ የኅብረተሰብ ክፍሎችን በመለየት የቅድመ ማስጠንቀቂያ መልክት ማስተላለፊያ ዘዴ መሆኑ ተገልጿል።

ስርዓት አደጋዎችን ለመከላከል እና የመታደግ ተግባራትን ለመፈፀም የሚጠቅም የቅድመ ማስጠንቀቂያ መልዕክት ማስተላለፊያ ዘዴ መሆኑን ነው የሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ያስታወቁት።

አጠቃቀሙ ቀላል እና ምቹ በመሆኑ ማኛውም አይነት ስልክ ያለው ዜጋ ተጠቃሚ እንዲሆን የሚያስችል እንደሆነም ሚንስትሯ ገልጸዋል።

ስርዓቱ የሙከራ ጊዜዉን በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናቶች ውስጥ አገባዶ ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ እንደሚገባም አስታውቅዋል።

ሚኒስቴሯ መቀመጫውን በጀርመን ሃገር ላደረገው ግሎባል አለርትስ እንዲሁም ሌሎች ስርዓቱ በስኬት ተጠናቆ ወደ ስራ እንዲገባ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ሁሉ ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ አለርት ሲስተም የተባለው ይህ የአደጋ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓት በሁለት ወገን በኩል መልዕክት የሚቀበል እና የሚልክ መሆኑ ፋይዳውን የበዛ እንደሚያደርገውም  ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.