የአለም ህዝብ ቁጥር ከ50 ዓመታት በኋላ እየቀነሰ እንደሚመጣ ጥናት አመለከተ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአለም ህዝብ ቁጥር ከ50 ዓመታት በኋላ እየቀነሰ እንደሚመጣ አንድ ጥናት አመለከተ።
በፈረንጆቹ 2064 የአለም ህዝብ 9 ነጥብ7 ቢሊየን የሚደርስ ሲሆን ሆኖም ግን በ2100 በ1 ቢሊየን ያህል ገደማ ቀንሶ 8 ነጥብ 8 ቢሊየን እንደደሚሆን ጥናቱ አመላክቷል።
የዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ይፋ እንዳደረጉት የሴቶች የትምህርት እና የእርግዝና መከላከያ ተደራሽነት በተሸለ መጠን መጨመር የውልደት መጠንን በከፍተኛ ደረጃ እየቀነሰ እንደሚሄድ ነው ጥናቱ የሚያመለክተው።
ጃፓንን፣ ታይላንድን፣ ጣሊያንን እና እስፔንን ጨምሮ የ23 ሀገራት የህዝብ ቁጥር ከ 50 በመቶ በላይ እንደሚቀንስ ተመራማሪዎቹ ገልፀዋል።
ሆኖም ከሰሃራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ ህዝቦች ቁጥር ሦስት እጥፍ ሊሆን ይችላል ያለው ጥናቱ ፣ ይህም ከዓለም ህዝብ ግማሽ ያህሉ እስከ ምዕተ-ዓመቱ መጨረሻ ድረስ አፍሪካዊያን እንዲሆን ያስችላል ብሏል።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።